በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የአራዳ ቀበሌ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ጊዜ ያለፈባቸውን የተለያያ አይነት የመጠጥ ምርት ሲሸጡ በተገኙ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ የገንዘብ ቅጣት እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ ።

ኃላፊው አክለውም ለነጋዴው ማህበረሰብ በተለያዩ ጊዜያት የንግድ አዋጅን መሠረት በማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የተሰጣ መሆኑን ገልፀው አሁንም አንዳንድ ነጋዴዎች ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶችን በተለያዩ ቦታዎች አከማችተው መገኛት ተስተውሏል በማለት ተናግረዋል ።

ጽ/ቤቱ አሁንም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደ ሆነ የገለፁት አቶ ዘመድኩን ዛሬ የተያዘው ጊዜ ያለፈባቸው የተለያዩ የመጠጥ ምርቶች ከ70 ደርዘን በላይ ሲሆን በቁጥር ከ840 በላይ መሆኑንም ገልጸዋል ።

እንድህ አይነት ድንገተኛ የቁጥጥርና ፍተሻ ስራ አሁንም ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው ያሉት ኃላፊው ለዚህም ተግባር የተለያዩ ኮሚቴዎችን ማደራጃታቸውንም አሳውቀዋል ።

በመጨረሻም ተጠቃሚው ህብረተሰብ ማንኛውንም ዕቃ ሲገዙ ጥንቃቄ በተሞላ መልኩ የጊዜ ገደብን በሚገባ አረጋግጠው መሆን እንዳለበት አሳስበው ነጋዴው ማህበረሰብም ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶችን በአግባቡ በማስወገድ የዜግነት ኃላፊነታቸውን በመወጣት ከአላስፈላጊ የወንጀል ድርጊት መታቀብ እንዳለባቸውም በአጽንኦት ገልፀዋል ።

 

Share this Post