የሆሳዕና ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል ዓመትና ከዚያ በላይ የሚፈጁ የክስ መዝገቦች ከሁለት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውሳኔ በመስጠት አበረታች እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ ።

በበጀት ዓመቱ የህብረተሰቡን የዳኝነት አገልግሎት ተጠቃሚነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በተቋሙ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶች በመለየትና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር የውሳኔ መዝገቦች በጥብቅ ዲሲፕሊን መምራት መቻሉ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ዳኛ ሙሉጌታ ጠቁመዋል ።

ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ በማዘመን በላቀ ደረጃ ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ዳኛ ሙሉጌታ በፍርድ ቤቱ ለሥራ አመቺ የሆኑ የችሎት አዳራሾች እና ቢሮዎች አለመኖር በአፈፃፀም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያስከተለ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል ።

Share this Post