21
Oct
2025
ከተማውን በማዘመንና ሁሉ አቀፍ የልማት ተደራሽነትን በማስፋት ለነዋሪዎቿ ለኑሮ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የልማት ማዕከል ለማድረግ በኮሪደር ልማት ስራዎችና አርንጓዴ ልማት ጥበቃ ተግባር ላይ በትኩረት እየሠራ ይገኛል በማለት ተናግረዋል ።
አቶ ደሳለኝ አክለውም በኮሪደር ልማት ባልተፈቀደ ቦታ ተሽከርካሪዎችን ማቆም፣እግረኞች ባልተፈቀደ ቦታ መንገድ ማቋረጥና በአጠቃላይ እየተሠራ ባለው መሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ከሚያደርሱ ማንኛውም ድርጊት ህዝቡ በመታቀብ ለደንብ አስከባሪዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል ።
ከደንብ አስከባሪዎች አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት የተሰጣቸው ተልዕኮ የከተማውን የልማት ስራ ከመጠበቅ በሻገር የከተማውን ሰላም በማስከበር ረገድም ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቅሰዋል ።
በዕለቱም የማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ደሳለኝ ደፋርን ጨምሮ የከተሞች ማስፈፀም አቅም ግንባታና ህብረተሰብ ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ተከተል ጩፋሞ፣የቦቢቾ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ትንሳኤ ታደሳ፣የጀሎናረሞ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያሲን ሁሴን እና የሴች ዱና ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ትልቁ ከበደና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።