የሆሳዕና የከተማው አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ በዞን ደረጀ 1ኛ በማግኘት ዋንጫና የምስክር ወረቀት ተሸላሚ መሆኑ ተገለፀ ።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ሰለሞን እንደገለፁት ጽ/ቤቱ ሽልማቱን ያገኘው በአጠቃላይ የፋይናንስ አሰራር የላቀ ውጤት ማስመዝገብ በመቻሉ ነው።

አክለውም ጽ/ቤቱ ያገኘው ሽልማት በአዲሱ የበጀት ዓመት ከዚህ የበለጠ ለመስራት የሚያነሳሳ በመሆኑ የፋይናንስ ደንብና መመሪያ በመከተል የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት እንደሚሰራም ኃላፊዋ ጠቁመዋል ።

በነስሩ ባደዢ

የሆሳዕና ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መስከረም 26/2018 ዓ.ም

Share this Post