21
Oct
2025
የአርሞንኤም ሁለተናዊ አገልግሎት የአገልጋዮች ህብረት ሰብሳቢ ፓስተር ሰላሙ ጫፋሞ እንደገለጹት ህብረቱ ድጋፍ ያደረገው ከአባላቱና ከተለያዩ በጎ አድራጊ ግለሰቦች ባሰባሰበው ገንዘብ ለእያንዳንዳቸው 1,500 (የአንድ ሺህ አምስት መቶ) ብር ድጋፍ አድርጓል ።
አክለውም ህብረቱ ቀደም ሲል በተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እገዛ ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀው በጎ አድራጊ ግለሰቦች በማስተባበር ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል ።
በነስሩ ባደዢ