የሆሳዕና ከተማ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከአርሞንኤም ሁለተናዊ አገልግሎት የአገልጋዮች ህብረት ጋር በመተባበር 40 ለሚሆኑ አካል ጉዳተኞች ከ60ሺህ ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ ።

የአርሞንኤም ሁለተናዊ አገልግሎት የአገልጋዮች ህብረት ሰብሳቢ ፓስተር ሰላሙ ጫፋሞ እንደገለጹት ህብረቱ ድጋፍ ያደረገው ከአባላቱና ከተለያዩ በጎ አድራጊ ግለሰቦች ባሰባሰበው ገንዘብ ለእያንዳንዳቸው 1,500 (የአንድ ሺህ አምስት መቶ) ብር ድጋፍ አድርጓል ።

አክለውም ህብረቱ ቀደም ሲል በተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እገዛ ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀው በጎ አድራጊ ግለሰቦች በማስተባበር ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል ።

በነስሩ ባደዢ

Share this Post