በትምህርት ሴክተር ሀገር ወዳድ በስነ ምግባር የታነጸ ዜጋ ማፍራት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል:

በክልሉ ከውጤት እና ከስነ ምግባር አንጻር ጠንካራ ተማሪ መፍጠር የውይይት መድረኩ አብይ የትኩረት አቅጣጫ ሊሆን እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።

የትምህርት ቤት አመራሮች፣መምህራን፣ወላጆች፣ተማሪዎች ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መስራት የሚችሉበትን ስርዓት መፍጠር ተገቢ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የተለየ ትኩረት ማድረግ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

የትምህርት ግብአት አቅርቦት ለዘርፉ እድገት ወሳኝ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የተጓደሉ ነገሮችን ለማሟላት የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል።

ዘገባው የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።

የሆሳዕና ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም

Share this Post