ዶ/ር ሀብታሙ በ2018 በጀት ዓመት በስንክሮናዜሽን ንቅናቄ ላይ ከ40 ሺህ በላይ ላሞችንና ጊደሮችን በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ ዘዴ በመጠቀም ከወለዱ 3 ወራት የምላቸውን የሀገረሰብ ድቃላ ላሞችንና ጊደሮችን በማዳቀል ከ22 ሺህ በላይ ጥጆች እንድወለዱ ለማድረግ ግብ በማስቀመጥ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ዮሐንስ እንዳሉት በሆርሞን የማድራት ቴክኖሎጅን በመጠቀም የዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያ ሥራ በአምስት ማዕከል ላይ ለተከታታይ አራት ቀናት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ጠቁመው በግብርና ሥራ የምርትና ምርታማነት ማነቆዎችን በመፍታት የቴክኖሎጅ አጠቃቀም በማሻሻል የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና ድህነትን ለማሸነፍ ሁለንተናዊ ተግባራትን እየሠራ እንደሚገኝ አብራርተዋል ።
አክለውም አቶ ጌታቸው የከተማ አርቢው ህብረተሰብ 1ኛ እርግዝና የሌላውን ላሞች 2ኛ ከወለዱ ከ3 ወር በላይ የሆናቸው ላሞች እና ለርቢ የደረሱ ግዳሮችን ከ4/01/2018 አስከ 8/01/2018 ዓ/ም ድረስ በአምስቱም ማዕከል ለይ ለተከታታይ አራት ቀናት የሚቆይ ሆርሞን የመስጠት አገልግሎት ሥራ እንደሚሰራ አሳስበዋል ።
በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የዞን ፣ የወረዳዎች ፣የከተማ አስተዳዳሮዎች፣የሁሉም ቀበሌያት አመራር አካላት የዞን ፣ የወረደ ፣ የከተሞች የእንሰሳትና ዓሣ ሀብብት ልማት ዘርፍ ባለሙያዎች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄዷል።