18
Oct
2025
በተጨማሪም አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ጽ/ቤቱ ለስራው የተመረጡ አመቺ የንግድ አካባቢዎችን በመለየት ዙሪያ በትኩረት እየተሠራ መሆኑንም አክለው ገልፀው የገበያ ትስስር ለመፍጠር ከተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እንደ ምሰራም ተናግረዋል ።
የሆሳዕና ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ምክትል ዲንና የዕለቱን የስልጠና ሰነድ ያቀረቡት አቶ ድሌቦ አባተ እንደገለፁት ተቋማቸው በተለያዩ የሙያ መስክ የክህሎት ስልጠና በሰፊው እየተሰጠ ነዉ በማለት ተናግረዋል።
በተለይም የንግድ ስራ በባህሪው የግልና የጋራ የቤተሰብ ምክክርና ፍላጎት ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት የገለፁት ኃላፊው ስልጠናው የሚሰጣቸው ተጠቃሚ ባለቤቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና ከመውሰዳቸው በፍት በፍላጎት ላይ የተመሠረተ ጥናት ልደረግ እንደሚገባም አሳስበዋል ።
በመጨረሻም የሆሳዕና ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የከተሞች ማስፈፀም አቅም ግንባታና የህብረተሰብ ተሳትፎ ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ስራ አስኪጅ አቶ ተከተል ጩፋሞ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ስራ ፕሮጀክት የአከባቢ ልማት ስራ ደንብና መመሪያ መርሆዎችን ለተሳታፊዎቹ በዝርዝር አቅርበዋል ።
ጌታቸው ደስታ
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ጥቅምት 08/02/2018 ዓ.ም