21
Oct
2025
በውይይቱ ላይ በከተማው በሊች አምባ ቀበሌ በፕሮጀክቱ የተገነባው የህፃናት ማቆያ ማዕከል ሥራ ለማስጀመር ፣የበሊሎ ወንጩሶ እና የቢር ዋቸሞ ት/ቤቶች ደረጃ ማሻሻያ ግንባታ ማካሄድ ፣አራዳ ለለውጥ የቁጠባና ብድር ተቋምና የአራዳ ማህበረሰብ አቀፍ መረዳጃ ዕድር ያሉባቸው ችግሮች መፍታት በሚያስችል ሁኔታ መግባባት ላይ መደረሱን ተገልጿል ።
በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በመንግሥት መሸፈን የማይችሉ የልማት ክፍተቶችን በመሙላት የሚያደርጉት ድጋፍ ቀላል ግምት የሚሰጠው አለመሆኑን በመግለፅ የፕሮጀክቱ ዕቅድ ለማሳካት አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ እንደሚደረግም ጠቁመዋል ።
በነስሩ ባደዢ
የሆሳዕና ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም