ፈጣንና አስደማሚ ዕድገት በክልሉ መመዝገቡ በመድረኮቹ የተነሳ ሲሆን፣ ለዚህም በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ህዝብ ሚና ከፍተኛ እንደነበርም ውይይት ተደርጎበታል።
በአጠረ ጊዜ ክልሉን የብልጽግና ተምሳሌትና የምርጥ ተሞክሮ መቀመሪያ ለማድረግ የሚያስችሉ ጠንካራ ስራዎች በየደረጃው እየተከናወኑ እንደሚገኙ አመራሮቹ በውይይታቸው አረጋግጠዋል።
የክልሉ አመራር ውጤት እያስመዘገበ እንዳለና ህዝቡም በአመራሩ ላይ ዕምነት እያሳደረ ስለመምጣቱም በመድረኮቹ ተነስቷል።
የተጀመሩ አጓጊና ተስፋ ሰጪ ስራዎችን በማጠናከር የክልሉን ህዝቦች ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ አመራሩ የስነ ልቦና አንድነት መፍጠር እንደሚገባውም ተብራርቷል።
በክልሉ በርካታ ድሎች እየተመዘገቡ ቢሆንም አንዳንድ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መሰረት በማድረግ በውስን አካባቢዎች ውዢንብር ለመፍጠር የሚደረጉ ጥረቶች እንዳሉም በመድረኮቹ ተነስቷል።
የክልሉ መንግስት ያደሩ የህዝቦች ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ያደረገውን ጠንካራ ጥረት የገመገሙት አመራሮቹ ፣የክልሉን ሰላም በማረጋገጥ በየአካባቢው የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰሩም አሳውቀዋል።
በመድረኮቹ ንካራ የፖለቲካ ስራ መስራት፣ በቂ ተግባቦት መፍጠር፣ የህግ የበላይነት ማረጋገጥ፣ የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲን ማጠናከር፣ የሰላ ትግል ማድረግ፣ ፍጥነትና ፈጠራ የታከለበት ስራ መስራት፣ ገዢ ትርክትን በመገንባት የህዝቦች አንድነትን ማጎልበት በድምሩም የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከጋራ መግባባት ተደርሷል።
በውይይት መድረኩ የአመራሩ፣ የአባሉና የህዝቡ ወቅታዊ ቁመና፣ አስቻይ ሁኔታዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።