24
Oct
2025
አክለውም በሴክተሩ ከሚተገበሩት ተግባራት አንዱ በሳይንስና ፈጠራ ሥራዎች ረገድ ችግር ፈቺ የፈጠራና የምርምር ውጤቶችን በማቅረብ በከተማው ከሚገኙ ት/ቤቶች መካከል የዋቸሞ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገቡ ጽ/ቤቱ በሽልማት ያገኘውን የፎቶ ኮፒ ማባዣ ማሽን ለት/ቤቱ በስጦታ ያበረከተ ሲሆን በት/ቤቱ ቀደም ሲል የፈጠራ ስራ ላከናወኑ መምህርና ተማሪ የማበረታቻ የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።
የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ታጋይ ዱቤ በሰጡት አስተያየት ጽ/ቤቱ ለት ቤ/ቱ ያበረከተው ስጦታ በቀጣይ ጊዜያት በተማሪዎችና በመምህራን የተሻለ የፈጠራ ስራዎችን ለማቅረብ የሚያነሳሳ በመሆኑ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
በነስሩ ባደዢ
የሆሳዕና ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ጥቅምት 14/2018 ዓ.ም