06
Nov
2025
የሀዲያ ዞን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሾመ አነሞ በበኩላቸው በሁሉም ቀበሌያት የብሄር ብሄረሰብ አከባበር ቅድመ ዝግጅትና በገቢ አፈጻጸም ላይ በጥንካሬ የታየውን ተግባራት በማስቀጠል አመራሩና ባለድርሻ ተቋማት ባለሙያዎች ተቀናጅቶ የአስተሳሰብ አንድነትን በማጠናከር ብልሹ አሰራሮችን በመቅረፍ ሌሎችንም ተግባራትን በታቀደው መሠረት ሀብት የማሰባሰብ ሥራ መስራት ይገባል ።
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አድነው ባፋ እንዳሉት አመራሩ በሁሉ ቀበሌያት የገቢ አሰባሰብ ተግባር አፈፃፀም ላይ የሚታዩ ውስንነቶች በልዩ ትኩረት በመስጠት በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር ሁል አቀፍ ሥራዎችን መስራት እንደሚጠበቅበት ጠቁመዋል ።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ጊዜ ሰጥተው ተግባራትን ቆጥሮ በመፈፀም የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል ።