በሆሳዕና ከተማ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያከናውኑዋቸው የልማት

በመድረኩ ላይ የፕሮጀክቱ የስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ በባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርጎበታል ።

የሆሳዕና ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ አድነው ባፋ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በልማት ሥራዎች የመንግስትን ክፍተት በመሙላት የሚጫወቱት ሚና ቀላል ግምት የሚሰጠው አለመሆኑን በመግለፅ በህፃናት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራው የፕሮጀክቱ ዓላማ እንዲሳካ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል ።

ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደር ሀዋሳ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ ደጀኔ በበኩላቸው የውይይት መድረኩ በፕሮጀክቱ ደካማ አፈፃፀሞች በማረምና ጠንካራ አፈፃፀሞችን በማስቀጠል በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ አጋዥ መሆኑን በመግለጽ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዳይለያቸው ጠይቀዋል።

የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ኤርሳሞ ባቾሬ እንዳሉት ፕሮጀክቱ በህፃናት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚያደርገው አበረታች ውጤታማ ለማድረግ በሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት ተሠጥቶት ሊታገዝ ይገባል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ፕሮጀክቱ ድጋፍ የሚሹ ቤተሰቦች አቅም በማጎልበት በህፃናት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ሥራ አበረታች መሆኑን በመግለጽ ድጋፋቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ።

Share this Post