06
Oct
2025
የመንግስት ተቋማትን በማጠናከር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከስሩ በማረም ተቋማቱን ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተግባራትን በማከናወን ግዴታቸውን ማውጣት እንደሚገባ በማሳሰብ ዜጎች የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋገጥና የብልፅግና ጉዞን ለማፋጠን በሀገራዊ ጥቅሞች የማይደራደር ስብዕናን በመላበስ መስራት እንዳለባቸው ተጠቁሟል ።
ዜጎች የኢትዮጵያን ከፍታ ለማረጋገጥና የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የተመዘገቡ ድሎችን ማስቀጠልና ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን እና ድሎቻችን ለማፅናት በአንድነት በመቆም እንደሚገባ የጋራ መግባባት ተፈጥሮ ።
ውይይቱም ወቅቱን የጠበቀና አሁናዊ ዓለም ዓቀፋዊ አህጉራዊና ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታን ለመገንዘብ ያስቻለ ስለመሆኑ ተሳታፊዋች አንስተው ከጂኦ-ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና ሀገራችንን ማሸጋገር ላይ የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት፣ አመራርና ሰራተኞች በጥልቀት በመወያየት ብሔራዊ ጥቅማችንን በሚገባ ከማስከበር አኳያ የተሟላ መግባባት ላይ በመድረስ የዕለቱ የውይይት ተጠናቋል ።
#አየለ ደልከሶ