የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ በዞን ደረጀ 1ኛ በማግኘት የምስክር ወረቀት ተሸላሚ መሆኑ ተገለፀ ።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ ስንታየሁ ምህርከ እንደገለፁት ጽ/ቤቱ ሽልማቱን ያገኘው በአጠቃላይ ሁለተናዊ የሴቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት የላቀ ውጤት ማስመዝገብ በመቻሉ ነው።

አክለውም ጽ/ቤቱ ያገኘው ሽልማት በአዲሱ የበጀት ዓመት ከዚህ የበለጠ ለመስራት የሚያነሳሳ በመሆኑ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት እንደሚሰራም ጠቁመዋል ።

በነስሩ ባደዢ

 

Share this Post