የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደ ።

የከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ደኛ ሙሉጌታ ከበደ በበኩላቸው ህብረተሰቡ ተገቢውን የፍትህ አገልግሎት እንዳያገኝና የፍርድ ሂደቱ እንዳይስተጓጓል በቀጣይ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥና ጥረት ያለው የወንጀል አፈታት እንዲኖር የሶስትዮሽ ውይይት ወሳኝ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ ተቋማቱ በአብሮነት ቅንጅት ፈጥሮ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ም/ኮ/ር ጥጋቡ ቀጭኔ እንዳሉት በቀጣይ በተገልጋዩ ህብረተሰብ ዘንድ ከፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ ብልሹ አሰራሮችንና ችግሮችን ለመፍታት በቁርጠኝነት ህገ ደንብን መሠረት በማድረግ ባለድርሻ ተቋማት በጋራ በመሆን ለለውጥ በቅንጅት በትኩረት ተግባራትን ማከናወን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ።

በመጨረሻም የከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ከከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት ጋራ ቀጣይ የሚተገበረው ተግባራትን ለማከናወን የሁለትዮሽ የስምምነት ፊርማ አኑረዋል ።

የምክክር ተሳታፊዎች የተሰጠው አስተያየት በሶስትዮሽም ሆነ በሁለትዮሽ ወንጀሎች እንዳይከሰት በቅንጅት ለመከላከልና ለዜጎች ፍትሐዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

Share this Post