በኮሪደር ልማት ስራ በየቀኑ ከአንድ ሺ በላይ ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል ወጣቶች ማግኘት መቻላቸውን ጠቁመዋል፡፡
አስተዳደሩ ከተማዋ ለስብሰባና ለቱሪዝም መዳረሻነት ተመራጭ እንድትሆን እየሰራ ነው ያሉት አቶ ሳሙኤል፤ በሰባት ቢሊዮን ብር ካፒታል የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም በከተማ አስተዳደሩ 24 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ፕሮጀክት እየተተገበረ ሲሆን፤ በተጨማሪም 20 ኪሎ ሜትር የሚሆን የውስጥ ለውስጥ መንገድ በግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።
በፌደራል መንግስት የሚሰራ 10 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር መንገድ መኖሩንም በማስታወስ፤ ሁሉም የመንገድ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ከተማዋን እጅግ ውብና ተመራጭ የሚያደርጓት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
አቶ ሳሙኤል ጨምረው እንደገለጹት፤ ሆሳዕና ከተማ የዘንድሮው 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል ይከበርባታል። ለዚህም ካለፈው ዓመት ጀምሮ በዓሉን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ የሚያስችሏት የልማት ስራዎች በመከናወን ለይ ይገኛሉ፡፡ ለአብነትም የስታዲያም እንዲሁም በርከት ያሉ መሰብሰቢያ አዳራሾች ግንባታ፣ የሆቴሎች የጥራት ደረጃ ማሻሻልና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ቅንጅታዊ ስራዎች እየተተገበሩ መሆናቸው ይጠቀሳል፡፡
ከመላው ሀገሪቱ ከአምስት ሺህ ሰው በላይ በዓሉን ለመታደም ይመጣሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ከ10 ሺ ያላነሱ እንግዶችም በውሎ ገብ ወደ ከተማ ይገባሉ ተብሎ በመታመኑ ይህንን በሚመጥን መልኩ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡