በሆሳዕና ከተማ ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደር ሀዋሳ ፕሮግራም አራዳ ፕሮጀክት በህፃናት ደህንነትና ጥበቃ ላይ ትኩረት አድርገው ለሚሰሩ ተቋማት ከ500ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የቢሮ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።

አክለውም ፕሮጀክቱ ድጋፍ ካደረጋቸው የቢሮ ቁሳቁሶች መካከል ጠረጴዛዎች ፣ሼልፎች ፣ኮምፒውተሮች ፣ፕሪተሮችና ወንበሮች እንደሚገኙበትም ጠቁመዋል ።

የሆሳዕና ከተማ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ስንታየሁ ምህርከ እንደገለፁት ተቋማቱ ድጋፍ በተደረገላቸው የቢሮ ቁሳቁሶች በመታገዝ ህፃናት ደህንነትና ጥበቃ ላይ የሚያከናወኑዋቸው ተግባራት ውጤታማ ለማድረግ መትጋት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል ።

Share this Post